የዊኪሚድያ ፋውንዴሽን የምርጫዎች ኮሚቴ/እጩዎች/2023/ማስታወቂያ - አዲስ አባላት
Appearance
አዲሶቹን የምርጫ ኮሚቴ አባላትን ማስታወቅ
ጤና ይስጥልኝ
አዲሶቹን የምርጫ ኮሚቴ አባላት እና አማካሪዎች ስናበስር በደስታ ነው። የምርጫ ኮሚቴው ለዊኪሚዲያ ፋውንዴሽን የአስተዳዳሪዎች ቦርድ በማህበረሰብ እና በአጋርነት የተመረጡ ባለአደራዎችን ለመምረጥ ሂደቱን በመንደፍ እና በመተግበር ላይ ያግዛል። ግልጽ የሆነ የእጩነት ሂደት ከተጠናቀቀ በኋላ ጠንካራ እጩዎች ከቦርዱ ጋር የተነጋገሩ ሲሆን አራት እጩዎች የምርጫ ኮሚቴውን እንዲቀላቀሉ ተጠይቀዋል። ሌሎች አራት እጩዎች በአማካሪነት እንዲሳተፉ ተጠይቀዋል።
ስማቸውን ለዕጩነት ያቀረባችሁ የማህበረሰብ አባላትን በሙሉ እናመሰግናለን። በቅርብ ጊዜ ውስጥ ከአስመራጭ ኮሚቴው ጋር እንደምንሠራ እንጠብቃለን።
በዊኪሚዲያ ፋውንዴሽን የአስተዳደር ቦርድ ስም ፣