የነጠላ የአባል መግቢያ ማጠቃለያ ማስታወቂያ

From Meta, a Wikimedia project coordination wiki
This page is a translated version of the page Single User Login finalisation announcement and the translation is 100% complete.
ስለዚህ ሂደት ወቅታዊ ዜና ለማግኘት mw:SUL finalisationን ይመልከቱ።

ለተጠቃሚዎቻችን አዳዲስ እና የተሻሉ መሣሪያዎችን ለማቅረብ ሲባል (ለምሣሌ ሁሉ ዊኪዎችን ያማከለ ማስታወቂያዎች) ፥ በዊኪሚድያ ፋውንዴሽን ያሉ የአጎልባቾች ቡድን የአካውንቶች አሠራር ላይ ለውጥ እያደረገ ነው። እነዚህን ለውጦች ለመደገፍ አባሎች ሁሉም ቦታ አንድ አካውንት ብቻ ሊኖራቸው ይገባል። ይህ ደግሞ ለማረም እና ለመወያየት የተሻሉ መሣሪያዎችን እና ለመሣሪያዎቹም ዘና ያለ የአባል ፍቃድ እንድንሰጥዎ ይረዳናል። ይህ እንዲሆን ደግሞ የአባላት አካውንቶች በሁሉም 900 ዊኪሚድያ ዊኪዎች ሁሉ ልዩ መሆን አንደኛው ቅድመ-ሁኔታ ነው።

ባሁኑ ጊዜ አንዳንድ አካውንቶች በሁሉም ዊኪአችን ላይ ልዩ አይደሉም ፤ ክፋቱ እንዚህ አካውንቶች ከሌላ ተመሳሳይ ስም ካላቸው አካውንቶች ጋር ይጋጫሉ። ሁሉም አባሎቻችን ወደፊት የዊኪሚድያን ዊኪዎች ተጠቃሚነታቸውን ለማረጋገጥ ፥ የነዚህ የአባሎች ስም "~" እና የዊኪአቸው ስም ከአባል ስማቸው መጨረሻ ላይ ይገባል። ይህ መካሄድ የሚጀምረው እ.ኤ.አ በሚያዝያ (ኤፕሪል) 2015 ይሆናል። ለምሣሌ፦ በስዊድንኛ ዊክሽነሪ ላይ ያለ "ምሣሌ" ተብሎ የሚጠራ አባል ቢኖር ስሙ "ምሣሌ~svwiktionary" ተብሎ ይቀየራል።

ሁሉም አካውንቶች እንደበፊቱ መሥራታቸውን ይቀጥላሉ ፤ እስካሁን ድረስ ያላቸውም አስተዋጽዖ መመዝገቡን ይቀጥላል። የአካውንት ስማቸው የተቀየረባቸው አባላት (በተናጠል እንገናኛቸዋለን) ለመግባት አዲሱን የአካውንት ስም መጠቀም ይኖርባቸዋል።

ተጠቃሚዎች ከአጠቃላይ ዊኪዎች እንዳይነጠሉ በማሰብ በአንድ ዊኪ ላይ ብቻ ስም መቀየር አሁን ቀርቷል። አባሎች አዲሱ ስማቸውን ካልወደዱት በአቅራቢያቸው ካለ ዊኪ ላይ Special:GlobalRenameRequestን በመጠቀም ወይም እዚህ በሜታ ላይ የብዕር ስማቸው እንዲቀየር መጠየቅ ይችላሉ።

ይህንንም ይመልከቱ