Fundraising 2010/Appeal/am

From Meta, a Wikimedia project coordination wiki

የዛሬ አስር አመት የውክፒዲያን ሃሳብ ሳነሳ ብዙወች አሾፉብኝ።

የአለም ህዝብ ተሰባስቦ፣ በፍፈቃደኝነት፣ እውቀትን ለማካፈል ሲባል ብቻ መዝገበ እውቀትን ይፈጥራል ብለው አንዳንድ የንግድ ሰወች ሊያስቡ አልቻሉም።

ማስታወቂያ የሌለው። ትርፍ የሌለው። አጀንዳ የሌለው።

ከተመሰረተ ከ፲ አመት በኋላ እነሆ ፫፻፹ ሚሊዮን ሰው በየወሩ ውክፒዲያን ይጠቀማል - ከኢንተርኔት ተጠቃሚ 1/፫ኛ ማለት ነው።

ውክፒዲያ ከአለም ፭ኛ ታዋቂ ድረገጽ ነው። ሌሎቹ ፬ቱ ድረገጾች በኩባንያወችና በቢልዮን ዶላሮች ሃይል ታግዘው የቆሙ ናቸው፣ ብዙ ተቀጣሪወች ያሏቸው ሲሆኑ በማያባራ መደለል ስራ የተሰማሩ ናቸው።

ውክፒድያ ግን እንዲህ አይደለም። በሰወች ማህበረሰብ የተፈጠርና፣ በፈቃደኞች ጽሁፍ አንድ ገጽ በአንድ ጊዜ እያለ የተመሰረተ ነው። እርስወም የዚህ ማህበርሰብ አካል ነወት። ዛሬ እምጽፍልወ ይህን ድረገጽ እንዲረዱና እንዲታደጉ ነው።

በትብብር፣ ይህን ድረገጽ ነጻና ከማስታወቂያወች የጸዳ ማድረግ እንችላለን። ስለሆነም መዝገበ እውቀቱን ክፍት - በፈለጉት መንገድ የሚጠቀሙበት ማድረግ እንችላለን። ማሳደግም እንችላለን - ዕውቀትን በሁሉ ቦታ በማሰራጨት፣ ከሁሉም ደግሞ ተሳትፎን በመጠየቅ።

በየአመቱ፣ በዚህ ወቅት ፣ እርስወንና ቀሪው የውክፒድያን ማህበረሰብ በገንዘብ እርዳታ እንዲረዱ እንጠይቃለን - ከተቻለወ $20, $35, $50 ወይም የበለጠ።

ውክፒድያ የመረጃወ ምንጭ አድርገው የሚያዩ ከሆነ - ጥሩ አነሳሽም ከሆኖ ካገኙት - አሁኑኑ እርምጃ እንደሚወስዱ ተስፋ አደርጋለሁ።

መልካሙን እየተመኘሁ፣

Jimmy Wales (ጂሚ ዌልስ)

የውክፒዲያ መስራች

ቀሪ ነጥብ፦ ውክፒድያ እንደኛ ያሉ ሰወች ከፍተኛ ነገርን ለመሰራት ያለንን ሃይል ይወክላል። እንደኛ ያሉ ሰወች ቃል-በ-ቃል አንድ ባንድ እያልን ውክፒድያን እንጽፋለን። እንደኛ ያሉ ሰወች ይደጉሙታል፣ አንድ ተዋጾ በአንድ ጊዜ። አለምን ለመቀየር ያለንን እምቅ ሃይል የሚይሳይ ነው።